ን ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ የማታና ተከታታይ ፕሮግራም በተፈጥሮ ሀብት፣ በእንስሳት ሳይንስ እና በእጽዋት ሳይንስ ሥልጠና ለመጀመር ዝግጅት አጠናቋል፡፡
ስለዚህ ምዝገባ 11/07/2015 ጀምሮ ለአምስት ተካታታይ የስራ ቀናት የሚካሄድ በመሆኑ፡- ትምህርት ፈላጊዎች ከ ደረጃ 1 እስክ ደረጃ 4 በማታ ና ቅዳሜና እሁድ መርሃ-ግብር በተፈጥሮ ሀብት፣ በእንስሳት ሳይንስ እና በእጽዋት ሳይንስ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፣
ለምዝገባ ስትመጡ ማሟላት ያለባችሁ መረጃዎች
- የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ውጤት
- 9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክርቢት
የክፍያ ሁኔታ፣ ለንድፈ ሀሳብ በሰዓት ለደረጃ 1 እና 2 ብር 6 (ስድስት ብር)፣ ለደረጃ 3 እና 4 ብር 8 (ስምንት)፣
ለተግባርና ለትብብር ስልጠና በሰዓት ለደረጃ 1 እና 2 ብር 7 (ሰባት ብር)፣ ለደረጃ 3 እና 4 ብር 9 (ዘጠኝ)፣
የማመልከቻ ማቅረቢያ ጊዜ፡ ከመጋቢት 11/2015 ዓ.ም እስከ መጋቢት 15/2015 ዓ.ም ነው፣
የመግቢያ ፈተና ከምዝገባ ብኋላ የሚገለጽ ሆኖ ለደረጃ 3 ፣4 እና 5 በ 2015 ወደ ኮሌጅ የመግቢያ ነጥብ እንድሁም የ 2014 1ኛ እና 2ኛ ዙር መግቢያ ውጤት መስፈርት መሰረት ይሆናል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0471353598 ዘወትር በስራ ሰዓት መደወል ይቻላል፡፡