ግንቦት 9/2016 ዓ.ም (ሚዛን ግብርና ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ)
የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥና አስተዳደር ሪፎርምን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሄደ
ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በተውጣጡ ባለሙያዎች እና የሚዛን ግ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ አመራሮች፣ መምህራንና አሰተዳደር ሰረተኞች በተገኙበት የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥና አስተዳደር ሪፎርምን በተመለከተ በሚዛን ግ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ ግቢ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሄደ፡፡
በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ ገለፃ የተደረገባቸው የፖሊሲ ዓምዶች ማሻሻያ ተግባራት፡
- የመንግሥት አስተዳደርና አደረጃጀት ሥርዓትን ማሳለጥ
- የመንግሥት ሠራተኞች የብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ሥርዓት መገንባትና የማስፈጸም አቅምን ማሳደግ
- ብዝኃነትንና አካታችነትን ያረጋገጠ ሲቪል ሰርቪስ ግንባታን ማፋጠን
- የዘመነ የመንግሥት ሠራተኞች የአስተዳደር ሥርዓትን መገንባት
- ቀልጣፋና ተደራሽ የመንግስት አገልግሎት አቅርቦት ሥርዓትን መዘርጋት
- የዲጂታል ሲቪል ሰርቪስ በመገንባት ቅቡልነት ያላቸው አገልግሎቶችንና ውሳኔዎችን ማቀላጠፍ
- የሲቪል ሰርቪስ ገቢር ነበብ አመራር እና ተቋም ግንባታን ማፋጠን
በመድረኩ ላይም የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥና አስተዳደር ሪፎርምን ማድረግ የተቋማትንና የሀገርን የወደፊት እጣ ፈንታ የመወሰን ጉዳይ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒሰቴር ባለሙያዎችና የሚዛን ግብርና ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ አመራሮች ገልፀዋል፡፡
ግንቦት 09/2016 ዓ.ም
ለወቅታዊና ትኩስ የሚዛን ግብርና ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ መረጃዎች፡
በድረገጽ፡- https://www.mizan-atvet.edu.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/mizan.atvet.facebook/
ቴሌግራም፦ https://t.me/mizanatvt