የ COC ምዘና ማስታወቂያ

በደረጃ 1 ፣ በደረጃ 2 እና ደረጃ 3 ከቀን 22/05/2015 እስከ 26/05/2015 ዓ.ም ድረስCOC ምዘና ለመውሰድ ሎግ ቡክ የሞላችሁ (የተመዘገባችሁ) ተማሪዎች በሙሉ የ COC ምዘና የሚሰጥበት ቀን በ 15/07/2015 ዓ.ም ስለሆነ፤ ይህንን አውቃችሁ ቅድመ-ዝግጅት እንድታደርጉ እያሳሰብን በተጠቀሰው ቀን የምዘና መግቢያ ስሊፕ ይዛችሁ እንድትገኙ በጥብቅ እናሳስባን፡፡

 
 

ን ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ የማታና ተከታታይ ፕሮግራም  በተፈጥሮ ሀብት፣ በእንስሳት ሳይንስ እና በእጽዋት ሳይንስ ሥልጠና ለመጀመር ዝግጅት አጠናቋል፡፡

ስለዚህ ምዝገባ 11/07/2015 ጀምሮ ለአምስት ተካታታይ የስራ ቀናት  የሚካሄድ በመሆኑ፡- ትምህርት ፈላጊዎች ከ ደረጃ 1 እስክ ደረጃ 4 በማታ ና ቅዳሜና እሁድ  መርሃ-ግብር በተፈጥሮ ሀብት፣ በእንስሳት ሳይንስ እና በእጽዋት ሳይንስ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፣

ለምዝገባ ስትመጡ ማሟላት ያለባችሁ መረጃዎች

  1. የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ውጤት
  2. 9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክርቢት

የክፍያ ሁኔታ፣  ለንድፈ ሀሳብ በሰዓት  ለደረጃ 1 እና 2  ብር 6 (ስድስት ብር)፣ ለደረጃ 3 እና 4 ብር 8 (ስምንት)፣

                  ለተግባርና ለትብብር ስልጠና በሰዓት ለደረጃ 1 እና 2  ብር 7 (ሰባት ብር)፣ ለደረጃ 3 እና 4 ብር 9 (ዘጠኝ)፣

የማመልከቻ ማቅረቢያ ጊዜ፡ ከመጋቢት 11/2015 ዓ.ም እስከ መጋቢት 15/2015 ዓ.ም ነው፣

የመግቢያ ፈተና ከምዝገባ ብኋላ የሚገለጽ  ሆኖ ለደረጃ 3 ፣4 እና 5 በ 2015 ወደ ኮሌጅ የመግቢያ ነጥብ እንድሁም የ 2014 1ኛ እና 2ኛ ዙር መግቢያ ውጤት መስፈርት መሰረት ይሆናል።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0471353598  ዘወትር በስራ ሰዓት መደወል ይቻላል፡፡

ቀን:  22/03/2015

 

የ COC ምዘና የተራዘመ መሆኑን ስለማሳወቅ

ደረጃ 3(III) እና ደረጃ 4(IV) በእንስሳት ሳይንስ፣ እፅዋት ሳይንስ እና በተፈጥሮ ሀብት የትምህርት ዘርፍ ለ COC ምዘና ሎግ የሞላችሁ በ ቀን 30/03/2015 ዓ.ም ምዘና እንደሚካሄድ ማስታወቂያ ያወጣን ቢሆንም ከ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ፕሮግራም መደራረብ ምክንያት የ COC ምዘና ቀን ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ ሲሆን ወደፊት የሚሰጥበትን ቀን በሌላ ማስታወቂያ የምናሳውቅ መሆኑን እንግልፃለን።

ከሠላምታ ጋር

 

 

የሚዛን ግብርና ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኮሌጅ